​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​

The power of freedom and unity

 Ethiopian Air Force

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​

  ​  ​​​​​​​የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ  

 አቪዬሽን ከጣልያን ወረራ በፊት ወደ ኢትዮጵያ ስለመግባቱ  

​​​​​
አቭዬሽን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው አገሪቱ ውስጥ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ልምድ ገና ሥር ባልሰደደበት ፣ የአገሪቱ የዕድገት ደረጃ ዝቅተኛ ሆኖ መሪዎቿ ለዘመናዊ ትምህርት ባልታደሉበትና ወደሥልጣኔ ሊያራምድ በሚችል ዕውቀት የተመሰረተ አመራር መስጠት በማይችሉበት ጊዜ ነበር ። ባመራር ላይ ከነበረው ከወግ አጥባቂው የመሳፍንቱና የባላባቱ ወገን ሌላ የቤተ ክርስቲያን ተፅዕኖም እማያላውስ ስለነበር ለአቪዬሽን ዕድገትና መስፋፋትየሚበጅ አስተሳሰብ ለነበራቸው ለራስ ተፈሪና ለጥቂቶቹ ተከታዮቻቸው ከባድ መሰናክል ነበር ። ያን ጊዜ አውሮፕላን በሰማይ ማብረር እንደሰይጣን ሥራ ፣ የእግዚአብሔርንም የበላይነት እንደመጋፋት ይቆጠር ስለነበር እንደራስ ተፈሪ ላሉ የጊዜው ተራማጅ መሪዎች እንቅፋት መሆኑ አልቀረም ። ስለሆነም ራስ ተፈሪ ይህን ሁሉ መሰናክል አልፈው በዚያን ጊዜ አውሮፕላን ወደ አገር ማስገባት መቻላቸው በሳቸው በኩል የተደረገውን የሚደነቅ ጥረት ያስረዳል ።
አውሮፕላን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባው በ1913 ዓም መሆኑ የተዘገበ ቢሆንም ይህ ወቅት አውሮፕላን ስለገባ አቪዬሽን ገባ ማለት እንዳይቻል ያደረገ ነበር ማለት ይቻላል ። ይኸውም በ1913 ዓም ሙሴ አቬል ባየር የተባሉ ፈረንሳዊ ሁለት የፈረንሳይ ሥሪት የሆኑ ብርጌ - 14 የተባሉ አውሮፕላኖች በሳጥን አሽገው አዲስ አበባ ድረስ በባቡር አስገብተው ነበር ። ሙሴ አቬል አውሮፕላኖቹን ያለማንም ፈቃድ ይዘው ለመግባት የወሰኑት ማንም ተቃውሞ አይኖረውም ብለው አስበው ይሁን ወይም ከአንዳንድ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች ጋር በቅድሚያ ተነጋግረው በመስማማት እንደሆነ የተገነዘበ መረጃ አልተገኘም ። በመንግስት ባለስልጣኖችና ቤተክርስቲያን አካባቢ ለቴክኖሎጂው ከነበረው ጠንካራ ተቃውሞ በተጨማሪ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩት የኢትዮጵያን ደካማነት የሚፈልጉ እንደ እንግሊዝ ፣ ፈረንሳይና ጣልያን የመሳሰሉት የውጪ ኃይሎችም ኢትዮጵያ ለአቪዬሽን ገና አልተዘጋጀችም ብለው የመንግስት ባለስልጣኖችን በማሳመን የራሳቸውን ፍላጐት ለማርካት መምከራቸው ለአውሮፕላኖች መመለስ ሌላው ምክንያት ነበር ::


 የመጀመሪያዋ አውሮፕላን ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት

​​​​​
በ1913ዓም የተከሰተው ሁኔታ ተገቢ አለመሆ  ኑን ባለሥልጣኖቻቸውንና ቤተክርስቲያንን በማሳመን በኢትዮጵያ የአቪዬሽን አገልግሎት እንዲተዋወቁና በሃገሪቱም ቦታ እንዲኖረው እጅግ ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ መሆናቸው አያከራክርም ። በ1920 ዎቹ አውሮፕላኖች እንዲገቡና በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያዊያን የአውሮፕላን አብራሪነት ፈቃድ እንዲሰጥ (የፓይለት ላይሰንስ) የፈቀዱና ሁኔታዎችን ያመቻቹ እሳቸው ነበሩ ። አቪዬሽን ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪገባ ለአጭር ጊዜም ቢሆን እንዲዘገይ ምክንያት የሆኑ ችግሮች ነበሩ ። ዋነኛው ምክንያት በከፍተኛ ዕውቀት የተመሰረተው ቴክኖሎጂ እንደ ኢትዮጵያ ባለው በሥልጣኔ ኋላ ቀር በሆነው ህብረተሰብ ውስጥ ትምህርት ባለመስፋፋቱ ዕውቀቱ ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ ጊዜ የፈጀ ቢሆንም ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ከብዙ አገሮች ቀዳሚ ሆና ትገኛለች ። ያም ሆኖ መለስተኝ ዘመናዊ አሰራሮችን ማስገባትና ሥራ ላይ ማዋል አዳጋች በነበረበት ጊዜ ይህ የረቀቀ ቴክኖሎጂ ውጤት ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ትልቅ እርምጃ ነበር ። ስለሆነም ራስ ተፈሪ ባደረጉት ጥረት አቪዬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው የራይት ብራዘርስ የተሳካ የአውሮፕላን በረራ ሙከራ ከተከናወነ ከ26 ዓመታት በኋላ ነሓሴ 12 ቀን 1921 ዓም ነው ።
 
ከፈረንሳይ “ሄንሪ ፖቴዝ አውሮፕላን ካምፓኒ” ከተባለ ኩባንያ ከተገዙ ፖቴዝ - 25 ከተባሉ 3 አውሮፕላኖች ውስጥ የመጀመሪያዋ ከጅቡቲ እየበረረት እሁድ ቀን አዲስ አበባ ገብታ ገፈርሳ በደህና ስታርፍ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአቬዬሽን ቴክኖሎጂ ተቋዳሽ ሆነች ። በራሪዋም ፈረንሳዊው አንድሬ ማዬ ነበር ። አውሮፕላኗ ገፈርሳ ስታርፍ የነበረው ደስታ ከፍተኛ ነበር ። “አቬሽን” በተሰኘው የሲቪል አቪዬሽን ልዩ የ1989 ዓም መፅሔት የመጀመሪያዋን አውሮፕላን መምጣት ደስታ ለመግለፅ “ፖቴዝ ተናገሪ” በሚል ርዕስ ከቀረበችው ግጥም ቅንጫቢ እነሆን ….


                        “ፖቴዝ ተናገሪ”
 
              ገፈርሳ የስድሳ አመቷ ገፈርሳ
              የሚግጥሽ የሚውልብሽ የቤት እንስሳ
              ላንድ ሳምንት እንዳይደርሱ ተከልክለው
              ቁጥቋጦው ባካፋ ፣ በዶማ ተምንግለው
              ካባጣ ጐርባጣው ተስተካክለሽ
              እንዳቅምሽ እንደባህልሽ ደግሰ
              ሆ ! ሎጋው ሽቦ እያሰኘሽ
              አይተሽ ያላወቅሽውን ሙሽራ አስተናገድሽ                    …….

​​

  የሁለተኛዋ አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት

​​​​​​
የመጀመሪያዋ አውሮፕላን በደረሰች በወሩ ጀንከርስ ድብልዩ - 33 የተባለችው ሙሉ ሰውነቷ እንደቆርቆሮ ያለ ቀላል ምረታ ብረት የተሰራ የጀርመን አውሮፕላን መስከረም 5 ቀን 1922 ዓም ከጅቡቲ በድሬዳዋ በኩል አዲስ አበባ በመግባት ሁለተኛዋ አውሮፕላን ሆነች ።
ከጀርመን የመጣችው ጁንከርስ አውሮፕላን ድሬዳዋ መጥታ ተገጣጥማ ወደ አዲስ አበባ እንድትበርና ፈረስ ግልቢያ ውድድር ይደረግበት በነበረው በጃን ሜዳ እንድታርፍ ተደረገ ። በራሪው ባሮን ቮን ኤንግል ሲሆን መካኒኩ ሽሚት ይባል የነበረ የጀርመን ተወላጆች ናቸው ።


  የአየር ኃይል መቋቋም ፅንሰ ሃሳብ መነሻ ምክንያቶች

​​​​
የታጠቀነአ የተደራጀ ጦር በኃይል አሰላለፍ ሚዛን ረገድ ሊያመጣ የሚችለውን ልዩነት ከጣልያን ወረራ በኋላ በግልፅ ማየት ስለተቻለ በተለይም አየር ኃይል ለድል ወሳኝነት በቅርብ በተግባር በመገንዘብ ትምህርት በመውሰድ ይህን ዘመናዊ የጦር ክፍል ለማቋቋም ብዙ ጥረት ተደረገ ። በ1928 ዓም የኢትዮጵያ ጦር ማይጨው ላይ ብዙ የተጐዳውና የተፈታውም በጠላት የአየር ጥቃት ነበር ። ስለ አየር ኃይል ወሳኝነት በማይጨው ጦርነት ጊዜ ..
በምስራቅ ቢመጣ ማን ያስገባው ነበር
በምዕራብ ቢመጣ ማን ያስገባው ነበር
በሰማይ መጣ እንጂ በማናውቀው አገር ።
ተብሎ የተገጠመው አዲስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተራቀቀ የመከላከያ ኃይል ማቋቋም እንደሚቻል ፣ እንደሚያስፈልግና እንዲሁም የአየር ጥቃት የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስገንዘብ ነው ።
ንጉስ ተፈሪ በአልጋ ወራሽነት ዘመናቸው በሕዳር 1914 ዓም በእንግሊዞች ግብዣ የመንን ጐብኝተው የእንግሊዝ አየር ኃይል ያዘጋጀውን አስደናቂ የአየር ትርዒት በተመለከቱበት ወቅት የአየር ኃይል አስፈላጊነት በአዕምሯቸው ተቀርፆ እንዲቀር ምክንያት ሆነ ።
ኢትዮጵያ ውስጥ አቪዬሽን በእግሩ መቆሙ የተረጋገጠው መስከረም 17 ቀን 1922 ዓም በተደረገው ሶስት አውሮፕላኖች በተሳተፉበት የመስከረም 16 የደመራ በዓል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው የበረራ ትርዒት ነው ።
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አነስተኛ የአቪዬሽን ትምህርት ቤት በ1922 ዓም በነበሩት ፖቴዝና ጁንከርስ አውሮፕላኖች አቋቋሙ ። የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን አብራሪዎች …

-አስፋው ዓሊ
-ሚሽካ ባቢቼቭ
-ስዩም ኃይለየሱስ
-ተስፋ ሚካኤል  …………… ነበሩ ።

እነዚህ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ቀዳሚ ፓይለቶች የመጀመሪያ ደረጃ የበረራ ትምህርታቸውን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ለተፈሪ መኰንን ንግስ ቀን በ1923 ዓም ብቻቸውን አውሮፕላን እየያዙ በኢትዮጵያ አየር ላይ ለመብረር ችለዋል ። በየጊዜው የሚገዙት ተጨማሪ አውሮፕላኖች በፍጥነትና በክብደት የተሻሉ እየሆኑ ጃንሜዳ ተስማሚ ሊሆን ስላልቻለ በዚህ ምክንያት ወደ ልደታ (አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ) እንዲዛወሩና ተግባራቸውን እዚያ ሆነው እንዲያከናውኑ ተደረገ ። እስከዚህ ድረስ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ፓይለቶች የሰለጠኑባት ታይገር ሞዝ የተባለችውን አውሮፕላን ጨምሮ 21 ከተለያየ አገር የተሰሩ አውሮፕላኖች ገብተዋል ።የጣልያን ወረራ በ1928 ዓም ሲጀመር ኢትዮጵያ የነበሯት አውሮፕላኖች 

​​​​​2 ቢችክራፍት ስታገርዊንግ - የአሜሪካ ስሪት የሆኑ በ1927 ዓም ተገዝተው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አውሮፕላኖች ናቸው​​​​

1 ብሬዳ ቢኤ 15 - የጣልያን ስሪት ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓም ለተከበረው የራስ ተፈሪ የንግስ በዓል በስጦታ መልክ ከጣልያን መንግስት የተላከች ።

1 ድሃቪላንድ . ዲ ኤች 60 ሞዝ - ይህቺ አነስተኛ አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ የገባችው ዓለም በአውሮፕላን የዞሩትና አፍሪካም ለመምጣት ካላቸው ፍላጐት ኢትዮጵያን መርጠው 1922/23 መግቢያ ላይ አዲስ አበባ ይዘዋት በገቡት በፈረንሳዩ ካውንት ጃክ ደ ሲቡር አማካኝነት ነው ። ከዚያ በኋላ አውሮፕላኗ የራስ ተፈሪን ሥልጣን ተቀናቃኞች በተለይም ራስ ጉግሳን ለመምታት በተደረገው እንቅስቃሴና ፁሁፎችን ከሰማይ በመበተን ተሳታፊ ሆናለች ።

1 ድሃኒላንድ ድራጐን (የመጀመሪያዋ የቀይ መስቀል አውሮፕላን)

1 ፋርማን 192 (ዘመናዊ ምቹ ሆና የተሰራች ለራስ ተፈሪ ጉግሳ በዓል ከፈረንሳይ በስጦታ የመጣች ሌላዋ አውሮፕላን)

1 ፋርማን 190 - እንደ ፋርማን 192 ሆና የተሰራች

1 ፊያት ኤ ኤስ-1 (ለማስተማሪያ ከጣልያን የመጣች በ 1922 አደጋ ደርሶባት የተሰባበረችና ከጥቅም ውጪ የሆነች)

2 ፎከር ኤፍ-ቪላ

1 ቢችክራፍት ቢ-17 ኤል - በ1927 ዓም ታጣፊ እግሮች ያሏት ባለሁለት ደረጃ መቀመጫ አሜሪካን ስሪት አውሮፕላን ከአሜሪካ ተገዝታ ወደ ኢትዮጵያ ገብታለች ። አብራሪ ሆነው የተመደቡት ሚሽካ ባቢቼቭ ሲሆኑ የአውሮፕላኗ ታጣፊ እግሮች አስቸጋሪ ስለሆኑባቸው ብዙ ሳትቆይ ረኔ ድሩሌ ለተባሉ የራስ ተፈሪ የግል ፓይለት በ 26’ 000 ማሪያ ቴሬዛ ብር ተሽጣለች ። ሬኔ ድሩሌ ይችን አውሮፕላን እስከገዙበት ጊዜ ድረስ የአፄ ኃይለስላሴ የግል ፓይለት ሆነው ይሰሩ ነበር ። ወደ አውሮፓም ለአውሮፕላን ግዢ እየተላኩ ያገለግሉ ነበር ።

1 ፎከር ኤፍ-11 ቢ/3ኤም - ይህች አውሮፕላን ራስ ተፈሪ ለግል ትራንስፖርት ይጠቀሙባት የነበረና በተጨማሪም ለቀይ መስቀል ሥራዎች ትሰማራ የነበረች ናት ።

1 ሄንክል ኤችዲ 21 - ለቀይ መስቀል ስራ የዋለች  

1 ጀንከርስ ደብልዩ 33ሲ - ጀንከርስ ድብልዩ 33ሲ ነሃሴ 30 ቀን 1921 ዓም ኢትዮጵያ የገባች የመጀመሪያ የግል አውሮፕላን ናት ። ባለቤቷ ሄር ዛህን የተባሉ ጀርመናዊ ፋርማሲስት ሲሆን አብራሪው ኤች ደብልዩ ቮን ኤንጅል ነበሩ ።

6 ፖተዝ-25 - መጀመሪያ ኢትዮጵያ የገባችውና የሷ ዓይነት ሌሎች 5 አውሮፕላኖች ናቸው

1 ዌበር ሚይንድል ቫን ኔስ ኤ VII (በኋል ኢትዮጵያ 1 የተባለችው)
 

Place title here
You can edit text on your website by double clicking on a text box on your website. Alternatively, when you select a text box a settings menu will appear. Selecting ‘Edit Text’ from this menu will also allow you to edit the text within this text box.
You can edit text on your website by double clicking on a text box on your website. Alternatively, when you select a text box a settings menu will appear. Selecting ‘Edit Text’ from this menu will also allow you to edit the text within this text box. 
 
Add Your Title Here
Add Your Sub-Title Here
This area is fully editable and gives you the opportunity to go into more detail about your business, what you do and what sets you apart from the competition. This area is fully editable and gives you the opportunity to go into more detail about your business, what you do and what sets you apart from the competition his area is fully editable and gives you the opportunity to go into more detail about your business, what you do and what sets you apart from the competition.
Button