ጄኔራሉና ያልከፈልነው ዕዳ

በዚህ የመጽሔት ስራ ውስጥ ትልቁን ሚና ከሚጫወት ወዳጄ የተደወለልኝን ስልክ ከአነሳሁ በኋላ ሌላ በዚሁ ስራ ላይ የበኩሉን ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ ወዳጃችን ተቀላቀለን ። ትልቁ እንግዳ የመጡት መጨረሻ ላይ ነው ።
ስናስባቸው ከርመን ነበር ። ስላለፈው ደግም ሆነ ክፉ ቀን ፣ ስለዛሬው ጥረታችንና ሰለወደፊት ተሰፋችን የሚሉትን ከአንደበታቸው ለማዳመጥ ጓግተናል ። ትሁትና ቅን ሰላምታ ተለዋውጠን ወደጉዳያችን ገባን ።
ብርጋዴር ጄኔራል አሸናፊ ገብረጻዲቅ ይባላሉ ። ዛሬ አሜሪካ ውስጥ በስደት ሲኖሩ አስራ ሁለት ዓመታትን አስቆጥረዋል ። በክፉ ቀን ኢትዮጵያን ከታደጓት የቀድሞው አየር ኃይል አባላት መሃከል አንዱና ግንባር ቀደሙም ናቸው ። በእኛ ዘመን ሃገሪቷ በይፋ ከመሰከረችላቸው ጥቂት ጀግኖች መሃከል በሕይወት ሰንብተዋል ። የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይ ተሸላሚው ጄኔራል ስለነገም ብሩህ አመለካከት አላቸው ። ወደፊት ለማየትም ወስነዋል ።
ጥያቄያችንን አሃዱ ብለን የጀመርነው አሁን በመቋቋም ላይ ስለአለው የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዓለም አቀፍ ሕብረት ነበር ። ምን ሃሳብ አለዎት አልናቸው ። መልሳቸው ወደፊት ለማየት ዝግጁ ከሆነ ሰው የሚጠበቅ ነበር ። እንዲህ አሉን ። “ይህ ትልቅ ዓላማ ነው ። ጅምሩን ወድጄዋለሁ ። እሰከአሁን በተሰራው ላይ አንድ እርከን የሚጨምር ነውና መበረታታ አለበት” … ፤ አሉና በሳል አመለካከታቸውን ጫን በማድረግ አከሉበት ።

ዝክረ ጀ/ል ለገሰ ተፈራ

1979 የበረራ ትምህርቴን ጨርሼ ከቀድሞዋ ሶቭየት ሕብረት ስመለስ ቀጣይ የበረራ ሙያዬን በኢትዮጵያው አየር ኃይል የበረራ ት/ቤት ቀጠልኩ ። የደብረ ዘይቱ የበረራ ት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ሶቭየት ሕብረት ከነበረው ሁኔታ እጅግ የተሻለ ሙያዊ ድባብ የተላበሰ ነበር ። ዙርያውን በአራት ማዕዘናት ተከቦ ከተሰሩት ቢሮዎች መካከል ከአንዱ ጠርዝ ላይ “ Reading Room” (መፃህፍት ቤት) የሚል ተመልክቼ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ ። መፃህፍት ቤቱ በተለያዩ ሰነዶችና መፃህፍት ተሞልቶ አገኘሁት ።
ዙርያውን ስቃኝ ደግሞ ከምዕራቡ የንባብ ክፍል ግድግዳ ላይ የምመለከተው አንዳች ነገር ስሜቴን ተቆጣጠረው ። በዝና እንጂ በአካል የማላውቃቸው ፣ ስማቸው አድማስን ተሻግሮ የገነነ ፣ የአየር ኃይሉ ዕንቁ በራሪዎች ፎቶ ግራፍ በስርዓት ተደርድረው ተመለከትኩ ። በ1969 በኢትዮ-ሶማልያ ጦርነት ወቅት የጠላትን አውሮፕላን በአየር ላይ በማጋየት ኢትዮጵያን የታደጉ ወደር ያልተገኘላቸው ጀግኖች ተብሎ በቀይ ደምቆ ተፅፏል ። በደስታ ሰውነቴን ሲነዝረኝ ተሰማኝ ። ተጣድፌ ስማቸውን ማንበብ ቀጠልኩ ……..

ኢትዮጵያ ውለታውን ከፍላ የማትጨርሰው ጀ/ል ለገሰ ተፈራ አረፉ !

ዛሬ ኦክቶበር 5 ቀን 2016 በማለዳው አሳዛኝ መርዶ ከወደ ዋሽንግተን ተሰማ ። እነሆ የአገራችንን የአየር ክልል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሲጠብቅና ሲያስከብር የኖረ ፤ ኖሮም በጀግንነቱ መላውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያኰራ አንድ ጀግና አረፈ መባሉን ከቤተሰባቸው ሰማን ።
ይህ አገር እንዲኖረን በመስዋዕትነቱ ያረጋገጠልን ጀግና ክንዱን መንተራሱ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ እጅግ አሳዛኝ ቀን ይሆናል ።
ጀነራል ለገሰ ተፈራ በመስዋዕትነቱ ያቆያት አገር በከፍተኛ ችግር ላይ ነች ። የጥቂቶች መፈንጭፋ ከሆነችም ሰነባበተች ። እስኪ ዛሬ ለእርሱ በአደባባይ የምትከፍለውን በአንድነት እናያለን ።

እውቁ የአየር ሰው ጄነራል ለገሰ ተፈራ በፅኑ ታመዋል

ጀነራል ለገሰ ተፈራ አየር ኃይልን በጦር አውሮፕላን በራሪነት ከተቀላቀሉ ወዲህ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች አመርቂ ውጤትን በማስመዝገብ በሰፊው ይታወቃሉ ።
በይበልጥ በ1969 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) ሶማልያ በዕብሪት የምስራቁንና የደቡብ ምስራቅ የአየራችንን ክፍል ስትወር የጄነራል ለገሰ ተፈራ አስተዋፅዖ ጉልህ ነበር ። በአየር ለአየር ውጊያ በርካታ የሶማሊያን የጦር አውሮፕላኖች በአየር ላይ ከማጋየታቸውም በላይ በተደጋጋሚ የምልልስ በረራዎች የአገራችንን የአየር ክልል እንዳይደፈር ያደረጉ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው ።

ከሕዝባችን ጋር የመወገን ባህላችን ይታደሳል

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህዝብ በተቆጣና ብሶቱን ማሰማት ሲጀምር ያለ አንዳች ማወላወል ከህዝብ ጋር የመወገንና የመቆም የቆየ ባህል አለው ። በቅድመ ቅንጅትና በኋላ እንደታየው አየር ኃይል አሰላለፉን ከህዝቡ ጋር ማስተካከሉና የህዝብ ወገን መሆኑን በተደጋጋሚ ያሳየበት ክስተት በቀላሉ ከአዕምሯችን ሊፋቅ አይችልም ።

ምርጫ 97 ትን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ እምቢተኝነት

- ሁለት Mi-35 አብራሪዎች እራሳቸውን ከስርዓቱ በማግለል ወደ ሱዳን
- ስምንት Su-27 ተዋጊ አውሮፕላን በራሪዎች ከቤለሩስ
- ሁለት Mi-35 ተዋጊ ሄሊኰፕተር በራሪዎች ወደ ጅቡቲ
- ሦስት የትራንስፖርት አውሮፕላን በራሪዎች ወደ ሱዳን
- አራት Su-27 እና የትራንስፖርት በራሪዎች ወደ ኡጋንዳ
- ሰባት የሰው አልባ አውሮፕላን ኦፐሬተሮች ከእስራኤል
- ሌሎችም እንዲሁ ከቻይና በተጨማሪም ከአገር ቤት ወደ ኤርትራ … ሄደዋል ።

ይህ እንግዲህ በቀላሉ አየር ኃይል የህዝብ መሆኑን የሚመሰክር ነው ። ህውሃት ደግሞ ይህንን የህዝብ ልጅነት ከስሩ ነቅሎ መጣል ይፈልጋል ። ሰራዊቱን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት ሌት ተቀን ይደግሳል ። በታጠቀው አውሮፕላን ሰላማዊ ዜጐችን እንዲያስፈራራና እንዲደበድብም ያስገድደዋል ። አየር ኃይል ህዝብን መደብደብ ባህሉ አይደለምና እንደማይታዘዘው አሳምሮ ያውቃል ። ስለዚህ ህውሃት ቅጥረኛ ባዕዳን በራሪዎችን በገዛ ዜጋው ላይ ያሰማራል ።

ጥሪ በህውሃት ስር እያገለገልክ ላለኸው የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት

ጥሪ በህውሃት ስር እያገለገልክ ላለኸው የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት

የአንድ አገር የመከላከያ ሰራዊት ዋና ተግባር የአገርን ብሄራዊ ጥቅም የማስጠበቅና በኃይል የመጣን የውጪ ወራሪ ኃይል በመመከት የአገርን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት ማስከበር እንደሆነ ይታወቃል ።
በዚህ በህውሃት የአገዛዝ ዘመን ግን ከላይ የጠቀስነውን ብሄራዊ ዓላማና ተግባር ማከናወን ሳይሆን በተቃራኒው የራሱን ሰላማዊ ዜጐች በማሸበርና በጐዳና ላይ ያለ ርህራሄ የጅምላ ፍጅት በመፈፀም ላይ መሆኑን ሁላችንም በከፍተኛ ሃዘንና ቁጭት እያስተዋልነው እንገኛለን ።
ላለፉት 25 ረጃጅም የሰቆቃ አመታት ህውሃት በዘር ተደራጅቶና በመሳሪያ አፈሙዝ በጉልበት ስልጣን ተቆናጦ በአገራችን ታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ዓለም ዓቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ህግጋትን በጣሰ መልኩ ሰላማዊ ዜጐችን ዒላማ ያደረገ የጭካኔ ፍጅት መፈፀሙን አጠናክሮ ቀጥሏል ። በዚህም የተነሳ ህዝባችን በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ከዚህ የጅምላ ፍጅት እራሱን በመከላከል ላይ ይገኛል ።

“ የህውሃት የውድቀት ሌጋሲ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ”

“እናንተ ዛሬ የአየር ኃይላችንን የጥራት መመዘኛ አሟልታችሁ በውጪ አገር ትምህርታችሁን ለመከታተል የምትሄዱ ወጣቶች ፤ በቅድሚያ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ። በቆይታችሁ ወቅትም ትምህርታችሁን በሚገባ ቀስማችሁ አገራችን ኢትዮጵያን ለማገልገልና ለህዝባችን ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት እንደሚኖርባችሁ ለአፍታም መዘንጋት
የለባችሁም ። ትልቅ አደራም ተሸክማችኋል ። ምንም እንኳ የከፋ ድህነት ያለባት አገር ዜጐች ብንሆንም
በአያት ፣ ቅድመ አያቶቻችን ተጋድሎና መስዋዕትነት የቀደምት ነፃነት ባለቤት አገር ዜጐች በመሆናችን እራሳችንን በኩራት ቀና አድርገን እንድንሄድ አስችሎናል ። በርከት ያሉ አገሮች ዜጐቻቸውን የሚያስተምሩበት ት/ቤት ውስጥ ከመጨረሻዎቹ ደሃ አገሮች መካከል ብንገኝም ጊዚያዊ የሆነውን ቁሳዊ ድህነትን ተቋቁሞ የአገር አደራን መወጣትን የመሰለ ታላቅ ክብር እንደ ሌለ ለኛ ለኢትዮጵያውያኖች ማንም ሊያስተምረን አይችልም ። በዕውቀት በልፅጋችሁ ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመማር ከጊዜው ጋር አብሮ ለመጓዝ የምትችል ኢትዮጵያን ለትውልድ የማስተላለፍ ክቡር የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ ።
ከሚገጥሟችሁ የብዙ አገር ተማሪዎች መካከልም ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች በዚሁ ት/ቤት ውስጥ ዜጐቻቸውን ያስተምራሉ ። ንቀት ፣ ጥላቻና ትንኰሳ ሊደረግባችሁ ይችላል ። እንደዚህ አይነት ሁኔታዎችን በተቻለ መጠን በትዕግስትና
በአስተዋይነት ማሳለፍ ያስፈልጋል ። ምክንያቱም አገራችሁ ከሰጠቻችሁ አደራና ከሄዳችሁበት ዓላማ በምንም መንገድ ዝንፍ ማለት አይገባችሁም ። እንዲህ ስላችሁ ግን የዜግነት ክብርን የሚነካ ፣ ህሊናን የሚያቆስል ትንኰሳ ከሆነ በምንም ዓይነት ዝም ብሎ ማለፍ አይገባም አፀፋውን መመለስ ይኖርባችኋል ። በዚህ ጉዳይ ለሚመጣ ማናቸውም ነገር ከጐናችሁ ነን ፤ መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንላችሁ”

ሜ/ጄ አምሃ ደስታ
ታህሳስ 1976 ዓም
ደብረ ዘይት - ሃረር ሜዳ

ጊዜው እንዴት ይሮጣል ? ይህ ከላይ ያነበባችሁትን ፅሑፍ ተወዳጁ የአየር ሰው ሜ/ጄ አመሃ ደስታ ከ32 ዓመታት በፊት እኔ አባል ለሆንኩበት ምልምሎች ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ለበረራ ስልጠና ከመሄዳችን አንድ ቀን ቀደም ብለው ሲሰናበቱን ያስተላለፉት መልዕክት ነበር ። ጊዜና ዘመን በማይሽረውና በማያደበዝዘው መልኩ ዛሬ ድረስ በልቤ ውስጥ ታትሞ ተቀምጧል ። እኚህ ታላቅ ጀነራል በመጨረሻም ቃላቸውን በመጠበቅ እኛን ስለአስተማሩን የዜግነት ክብር ነፍሳቸውን አሳልፈው ሲሰጡ ለመታዘብና ለመመስከር በቃሁ ። መቼም
ቢሆን የማይረሳ ፣ የማይዘነጋ ፣ ድንቅና ህያው ታሪክ ።

Pages